የቃል ክርክር እንድታደርጉ ስለማሳወቅ

አመልካች የደስታ ቡና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማሕበር በማመልከቻ ቁጥር LTM/12993/2022 ዓለም አቀፍ ምድብ 35 YEDESTABUNA  የሚል የቃል እና የምስል የንግድ ምልክት ለማስመዝገብ ማቅረቡንና ከዚህ ቀደም በማመልከቻ ቁጥር  LTM/0048 ከተመዘገበ  Desta ከሚል የንግድ ምልክት ጋር ይመሳሰላል በሚል ውድቅ በማድረግ የስራ ክፍሉ የሰጠው ውሳኔ አግባብ አይደለም በሚል የቀረበ የአቤቱታ ማመልከቻ ላይ አመልካች እና ጣልቃ ገብ (ደስታ አልኮልና መጠጦች ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ) በቀን 22/09/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት በባለስልጣን መ/ቤቱ አዳራሽ (2ኛ ፎቅ) በመገኘት የቃል ክርክር እንድታደርጉ ተቀጥሯል፡፡

የአእምሯዊ ንብረት ትሪቡናል