አመልካች ሪሂኖ ኬብል ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በማመልከቻ ቁጥር LTM/14262/15በተጠሪ ሪይኖ ትራዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ስም ተመዝግቦ የሚገኘው የሚለው የቃል እና የምስል የንግድ ምልክት ፈራሽ ሊሆን ይገባል በሚል የቀረበ የፈራሽነት ማመልከቻ ላይ አመልካች እና ተጠሪ በቀን 29/09/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 በባለስልጣን መ/ቤቱ አዳራሽ (2ኛ ፎቅ) በመገኘት የቃል ክርክር እንድታደርጉ ቀጠሮ ተሰጥቶ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ሆኖም አመልካች በዚሁ ቀን (በ 29/09/2016 ዓ.ም) በፅሁፍ ባቀረበው ማመልከቻ የነበራቸው የህግ ባለሙያ በገጠመው ችግር ምክንያት አዲስ የህግ ባለሙያ (ጠበቃ) ለማቆም ውክልና መስጠት እና ጠበቃውም በጉዳዩ ላይ ዝግጅት የሚያስፈልገው በመሆኑ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
በመሆኑም ከላይ በተጠቀሰው መዝገብ ላይ አመልካች እና ተጠሪ በቀን 06/10/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 በባለስልጣን መ/ቤቱ አዳራሽ (2ኛ ፎቅ) በመገኘት የቃል ክርክራቸውን እንዲያቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጠ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአእምሯዊ ንብረት ትሪቡናል
